Home   |   Ethiopia  | Ethiopian News  The Embassy Consular/Visa  |  Tourism  |   Trade   | Investment  |  Community  | Links

ማስታወቂያ
Announcement

 

 ማስታወቂያ

ለአገልግሎት ጠያቂዎች በሙሉ

 

በስቶክሆልም የሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ ፅ/ቤት ከመስከረም 01 ቀን 2003 ዓም ጀምሮ የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያና ለውጥ ያደርጋል፡፡

በመሆኑም ማንኛውም ተገልጋይ ወደ ቆንስላ ፅ/ቤቱ በአካል ከመምጣቱ በፊት ለሚፈልገው ማንኛውም ግልጋሎት በቆንስላ ጽ/ቤቱ የተዘጋጀውን የአገልግሎት መስጫ ቅፅ በቅድሚያ ከቆንስላ ጽ/ቤቱ ድረ-ገፅ www.ethemb.se በማውጣት በመሙላት ይዞ መቅረብ ይጠበቅበታል፡፡

የኢትዮጵያ ኤምባሲ

ስቶክሆልም

 

 

Ethiopian Embassy in Stockholm, Sweden is also Accredited to Denmark, Finland, Iceland, Norway.

 

ለማንኛውም አገልግሎ ክፍያ በስዊድን ክሮነር መፈፀም የሚኖርበት ሲሆን ክፍያው በኤምባሲው Postgiro No. 629247-8 ወይም የባንክ አካውንት (Nordea Bank IBAN No. SE62 9500 0099 6026 0629 2478, SWIFT-Code NDEASESS) ተገልጋዩ ወደ ቆንስላ ፅ/ቤቱ ከሚመጣበት ቀን ከ5 ቀን አስቀድሞ ከፈል ይኖርበታል፡፡

 

Visiting address:

Ethiopian Embassy
Löjtnantsgatan 17, 5th floor
115 50 Stockholm, Sweden

 

Contact Address:

Telephone: +46-8-6616325

Fax: 004686608177
Email:
ethemb.community@telia.com

website: www.ethemb.se,

 

 

 

Office Hours for consular section

 

Visiting Hours:       between 09:00 to 12:00 Monday to Friday.

 Telephone Hours: between 13:30 - 15:30 Monday to Friday

 

Announcement

 

The Ethiopian Consulate Office in Stockholm will change its procedures of service delivering as of September 11, 2010.

Therefore, all applicants who are coming in person to the Consulate office for any service should have to fill the application form in advance for their required services. Application forms can be found on the Consulate office website, which is www.ethemb.se.

Ethiopian Consulate

Stockholm

 

ማስታወቂያ

በውጭ ነዋሪ የገቢ ግብር ከፋዮች በሙሉ

 

በአገራችን የታክስ አከፋፈል ስርአትን ቀልጣፋና ዘመናዊ ለማድረግ ይቻል ዘንድ ማንኛውም በኢትዮጵያ ውስጥ በግብር ከፋይነት የሚታወቅ ግለሰብ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2002 ዓም ሀገር ውስጥ በአካል በመገኘትና የጣት አሻራ በመስጠት የታክስ ሰርቲፊኬቱን መውሰድ እንዳለበት መመሪያ መውጣቱ ይታወሳል፡፡

ይሁን እንጂ በተለያዩ ችግሮች ምክንያት በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ኢትዮጵያ ገቢዎች ባለስልጣን በአካል በመቅረብ የጣት አሻራ በመስጠት የታክስ ሰርቲፊኬት መውሰድ ያልቻሉ ኢትዮጵያውያንና ትውልድ ኢትዮጵያውያን በጠየቁት መሰረት ቀን ገደብ ወደ ታህሳስ 30 ቀን 2003 ዓም እንዲራዘም ተደርጓል፡፡

በመሆኑም ቀደም ሲል ኤምባሲ ባወጣው ማስታወቂያ መሰረት የጣት አሻራ ለመስጠት የተመዘገባችሁ እንዲሁም እስካሁን የታክስ መለያ ቁጥር ያልወሰዳችሁና በአገር ቤት በምታንቀሳቅሱት ቋሚ ወይም ቋሚ ያልሆኑ ንብረት በማንቀሳቀስ ግብር ከፋይ የሆናችሁ በሙሉ ቀነገደቡ ከመጠናቀቁ በፊት ኢትዮጵያ ገቢዎች ባለስልጣን በአካል ቀርባችሁ ጣት አሻራ በመስጠት እስከ መጋቢት 30 ቀን 2003 ዓም ባለው ጊዜ ውስጥ የታክስ መክፈያ ሰርቲፊኬቱን መውሰድ እንደሚገባችሁ ባለስልጣን መ/ቤቱ በድጋሜ ማስታወቁን እናስገነዝባለን፡፡

በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ በአካል ቀርበው የጣት አሻራ በመስጠት የታክስ መክፈያ ሰርቲፊኬት ያልወሰዱ የንግድ፣ የኢንቨስትመንት እና ሌሎች ማናቸውም ገቢ ግብር የሚከፈልባቸው ፍቃዶች የሚሰረዙ መሆኑን ባለስልጣን መ/ቤቱ ጨምሮ መግለፁንም በአክብሮት እንገልፃለን፡፡

ተጨማሪ መረጃ

· በስልክ ቁጥር  004686616158 ወይም በኢሜል ethemb.community@telia.com ወይም ስቶክሆልም በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በአካል በመቅረብ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በጣት አሻራ የተደገፈ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር አሰጣጥ አጭር ማብራሪያ

 

የኢትዮጵያ ኤምባሲ

ስቶክሆልም

 

ማስታወቂያ

በቤት ማህበር ለተደራጁ

የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልድ ኢትዮጵያውያን በማህበር ተደራጅተው የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ የሰጠ ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች ከ1997 ዓም ጀምሮ እንዲቆም መደረጉ የሚታወስ ነው፡፡

ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት መስተዳደሩ በማህበራት ተደራጅተው በመጠባበቅ ላይ የሚገኙ ማህበራትን ደረጃ በደረጃ ለማስተናገድ በያዘው እቅድ መሰረት ቀደም ሲል በቤት ማህበራት ተደራጅታችሁ፣ ተገቢውን ፎርማሊቲዎች አሟልታችሁ፣ ሰነዶቻችሁ ወደ አዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ከተላኩ በኋላ በዝግ አካውንት ገንዘብ ያስቀመጡ ማህበራት ዝርዝር እንዲላክ ከመስተዳደሩ ጥያቄ የቀረበ በመሆኑ   በዝግ አካውንት ገንዘብ ያስቀመጣችሁ ማህበርት በዝግ አካውንት ገንዘብ ያስቀመጣችሁበትን የሚያረጋግጥ ሰነድ በማቅረብ በአስቸኳይ እንድትመዘገቡ በአክርሮት እናሳስባለን፡፡

የኢትዮጵያ ኤምባሲ

ስቶክሆልም

 

ማስታወቂያ

የግልና የቤት ውስጥ መገልገያዎችን ቀረጥ ክፍሎ ስለማስገባት

ነሀሴ 12 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም

በውጭ  የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልድ ኢትዮጵያውያን ወደሀገራቸው ጠቅለው ሲመለሱ ኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን መ/ቤት አሻሽሎ ባወጣው መመሪያ መሰረት በሚኖሩበት አካባቢ ከሚገኝ የኢ...ሪ ኤምባሲ አመልካቾች በውጭ ሀገር አምስት አመትና ከዚያ በላይ መቆየታቸውንና ወደሀገራቸው ጠቅለው  ሀገር የሚመለሱ መሆናቸውን በማረጋገጥ የድጋፍ ደብዳቤ በሚሰጥበት ጊዜ ብቻ የግልና የቤት ውስጥ መገልገያዎችን ቀረጥ ክፍለው ማስገባት እንዲችሉ ሲደረግ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

ይሁን እንጂ አንዳንድ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልድ ኢትዮጵያውያን ተሽከርካሪን ጨምሮ የግል የቤት ውስጥ መገልገያዎችን ቀረጥ እስከተከፈለ ድረስ ማስገባት ይቻላል በሚል የተሳሳተ መረጃ ያለምንም ቅድመ-ሁኔታ ማስገባት እንደሚችሉ በመገመት ዕቃዎቻቸውን ይዘው አገር ቤት በመሄድ ችግር እየገጠማቸው እንደሚገኝ ለመገንዘብ ተችሏል፡፡

ስለሆነም ቀረጥ ከፍሎ የማስገባት መብት ያላቸው ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ብቻ መሆናቸውን እየገለጽን በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልድ ኢትዮጵያውያን ቀረጥ ከፍለው ማስገባት የሚችሉት ከሚኖሩበት ሀገር አምስት አመትና ከዚያ በላይ መቆየታቸውን በሚገባ የሚያረጋግጥ ተጨባጭ ሰነድ አቅርበውና ጠቅልለው ወደሀገራቸው ሲመለሱ ብቻ በኤምባሲው በሚሰጥ የድጋፍ ደብዳቤ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

  የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ኤምባሲ

ስቶክሆልም

 


www.ethemb.se | ©2006 Embassy of FDRE All Rights Reserved | ethemb.all@telia.com| ethemb.community@telia.com