VISA AND OTHER CONSULAR SERVICES

Visa  |  Passport   Ethiopian Origin ID   Certificate of National Identity   |  Laissez Passer   Legalisation   Duty and Duty Free

Duty and Duty Free

 

 

ማስታወቂያ

ነሀሴ 12 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም

በውጭ  የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልድ ኢትዮጵያውያን ወደሀገራቸው ጠቅለው ሲመለሱ ኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን መ/ቤት አሻሽሎ ባወጣው መመሪያ መሰረት በሚኖሩበት አካባቢ ከሚገኝ የኤፌድሪ ኤምባሲ ወደሀገራቸው ጠቅለው የሚመለሱ መሆናቸውን በማረጋገጥ የድጋፍ ደብዳቤ በሚሰጥበት ጊዜ ብቻ የግል የቤት ውስጥ መገልገያዎችን ቀረጥ ክፍለው ማስገባት እንዲችሉ ሲደረግ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

ይሁን እንጂ አንዳንድ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልድ ኢትዮጵያውያን ተሽከርካሪን ጨምሮ የግል የቤት ውስጥ መገልገያዎችን ቀረጥ እስከተከፈለ ድረስ ማስገባት ይቻላል በሚል የተሳሳተ መረጃ ያለምንም ቅድመ-ሁኔታ ማስገባት እንደሚችሉ በመገመት ዕቃዎቻቸውን ይዘው አገር ቤት በመሄድ ችግር እየገጠማቸው እንደሚገኝ ለመገንዘብ ተችሏል፡፡

ስለሆነም ቀረጥ ከፍሎ የማስገባት መብት ያላቸው ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ብቻ መሆናቸውን እየገለጽን በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልድ ኢትዮጵያውያን ቀረጥ ከፍለው ማስገባት የሚችሉት ከሚኖሩበት ሀገር ጠቅልለው ወደሀገራቸው ሲመለሱ ብቻ በኤምባሲው በሚሰጥ የድጋፍ ደብዳቤ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

 

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ኤምባሲ

ስቶክሆልም

 

ጥቅምት 2ዐ ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም.

ማስታወቂያ

ቀደም ሲል በውጭ አገር ኖረው ወደ ሀገራቸው ጠቅልለው የሚመለሱ ኢትዮጵያውያንና ትውልድ ኢትዮጵያውያን መኪናን ጨምሮ የቤት ውስጥ መገልገያዎችን ከቀረጥ ነፃ እንዲያስገቡ የሚፈቅድ አሰራር ተግባራዊ ሲደረግ ቢቆይም አንዳንድ ተገልጋዮች የተሰጠውን እድል አለአግባብ በመጠቀማቸው ምክንያት እንዲቆም መደረጉ ይታወሳል፡፡

ይሁን እንጂ የቀረጥ ነጻ እድሉ እንዲቆም ሲደረግ ቀረጥ ከፍሎ ማስገባት የሚቻልበት አሰራር አብሮ የቆመ ባለመሆኑ በውጭ አገር አምስት ዓመትና ከዚያ በላይ ቆይተው ወደ ሀገር ጠቅልለው የሚመለሱ ኢትዮጵያውያን ብቻ መኪናን ጨምሮ ሙሉ የቤት ውስጥ መገልገያ መሣሪያዎችን ቀረጥ ከፍለው ማስገባት የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ኤምባሲ

ስቶክሆልም

 

ቀረጥ ከፍሎ ማስገባት መሟላት የሚገባቸው

  • የአመልካች ማመልከቻ

  • አምስት ዓመትና ከዚያ በላይ መቆየትን የሚያረጋግጥ ሰነድ

  • ወደ ሀገር ጠቅልለው የሚመለሱ መሆኑን ማረጋገጫ ሰነድ

 

የግልና የቤት ውስጥ መገልገያ ዕቃዎችን በልዩ መብት በታክስና ቀረጥ ማስገባት ስለሚቻልበት ሁኔታየግልና የቤት ውስጥ መገልገያ ዕቃዎችን በልዩ መብት ከታክስና ከቀረጥ ነፃ ወይም በታክስና ቀረጥ ለማስገባት የባለመብቶቹ አመዳደብና የሚያስገኛቸው የቀረጥ ነፃ መብቶች

በቀረጥና ታክስ ነፃ ተጠቃሚ ለመሆን አመልካቾች ማሟላት የሚጠበቅባቸው መረጃዎች

 

1.   ኢትዮጵያውያን (ቋሚ የመኖሪያ ፍቃድ ያላቸው ወይም ጊዜያዊ የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸው ወይም በስደተኛ ካምፕ የሚኖሩ)፣

1.1.  ኦሪጅናል ፓስፖርት

§      ገፅ 1 (ለአዲሱ ፓስፖርት) ወይም ከገጽ 1-7 እና የቅርብ ጊዜ ዕድሣቱን የሚያሳየውን ገጽ ኮፒ (ለድሮው ፓስፖርት)፣

§       ስደተኛ ከሆኑ ከፖሊስ ወይም ከኢሚግሬሽን የተሰጠ የምዝገባ መረጃ፣

§       ተማሪ ከሆኑ ከገጽ 1-7 እና የቅርብ ጊዜ ዕድሣቱን የሚያሳየውን ገጽ እና በፓስፖርቱ ላይ ተማሪነትዎን የሚያሳይ የመኖሪያ ፍቃድ ያለበት ገጽ ኮፒ ሁሉም፣

1.2.  ከሚኖሩበት አገር ከታክስ ባለሥልጣን የቆይታ ጊዜን የሚያሳይ መረጃ፣

1.3.  ተማሪ ከሆኑ ትምህርትዎን ከተከታተሉበት (የትምህርት ዕድል እንደተሰጠዎት የሚያሳይ፣ ትምህርትዎን እንደሚያጠናቅቁ ወይም ማጠናቀቅዎትን የሚገልጽ ሆኖ የጀመሩበትና ያጠናቀቁበትን ጊዜ የሚያሳይ) ማስረጃ፣

1.4. ከኢትዮጵያ በግል የስራ ዕድል አግኝተው የስራ ጊዜዎን ጨርሰው/አቋርጠው የሚመለሱ ከሆነ ከሰሩበት መ/ቤት የሰሩበትን ጊዜ የሚያሳይና ባሉበት አገር ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጠ መረጃ፣

1.5.  ጠቅለው የሚመለሱ ከሆነ

§  ጡረተኛ - የጡረታና ከታክስ ባለሥልጣን የቆይታ ጊዜን የሚያሳይ መረጃ፣

§   ሌሎች - ቋሚ የመኖሪያ አድራሻ (Registration of moving abroad) መቀየራቸውን የሚያሳይና ከታክስ ባለሥልጣን የቆይታ ጊዜንና አዲሱን አድራሻ የሚያሳይ መረጃ፣

2.      የኢትዮጵያ ተወላጅ መታወቂያ ካርድ የያዙ

2.1.  ከፓስፖርት ውስጥ ፎቶግራፍ የሚገኝበት ገጽ ኮፒ፣

2.2.  የኢትዮጵያ ተወላጅ መታወቂያ ካርድ ኮፒ፣

2.3.  ጠቅለው የሚመለሱ ከሆነ

§    ጡረተኛ - የጡረታና ከታክስ ባለሥልጣን የቆይታ ጊዜን የሚያሳይ መረጃ፣

§    ሌሎች - ቋሚ የመኖሪያ አድራሻ (Registration of moving abroad) መቀየራቸውን የሚያሳይና ከታክስ ባለሥልጣን የቆይታ ጊዜንና አዲሱን አድራሻ የሚያሳይ መረጃ፣

ማሳሰቢያ:-

v በስዊድን ነዋሪ የሆኑ የሚላክላቸውን የቀረጥና ታክስ ከፍሎ ማስገባት መብት ተጠቃሚ ለመሆን የሚያስችላቸውን ደብዳቤ መላኪያ፣ የመመለሻ አድራሻ የተዘጋጀበት ባለ 65 ክሮነር ስታምፕ የተለጠፈበት የተዘጋጀ ፖስታ አብሮ መላክ፣

v ከስዊድን ውጭ የሚኖሩ የሚላክላቸው የቀረጥና ታክስ ከፍሎ ማስገባት መብት ተጠቃሚ ለመሆን የሚያስችላቸውን ደብዳቤ መላኪያ፣ የመመለሻ አድራሻ የተዘጋጀበት ፖስታና የ1ዐዐ ክሮነር የተመጣጣኝ የሆነ ዋጋ ያለው ኢንተርናሽናል ኩፖን መላክ ይኖርባቸዋል፡፡

The Application Form

(pdf)
(jpg)

 

 

Postal Address

Embassy of the Federal Democratic Republic of Ethiopia

P. O. Box 10148
100 55 STOCKHOLM, SWEDEN

 

 

E-mail

ethemb.community@telia.com

 

Telephone hours

13:00 PM - 15:30 PM HRS

Tel.004686616158 

(For Duty and Duty free issues)

 

Visiting hours

9:00 AM - 12:00 AM (Visiting hours) 

 

 

 


www.ethemb.se | ©2006 Embassy of FDRE All Rights Reserved | ethemb.all@telia.com  | ethemb.community@telia.com