27ኛው የግንቦት 20 በዓል እንዲሁም 7ኛው የህዳሴ ግድብ መሠረት የተጣለበት በዓል ሜይ 6 እና 12 ቀን 2018 በዴንማርክ እና በስቶክሆልም ከተሞች ተከብሯል፡፡

6.5ሚሲዮናችን ከስቶክሆልምና የዴንማርክ የህዳሴ ምክር ቤት ጋር በመተባበር 27ኛው የግንቦት 20 በዓል እንዲሁም 7ኛው የህዳሴ ግድብ መሠረት የተጣለበት በዓል ከ200 በላይ ኢትዮዽያውያንና ትውልደ ኢትዮዽያውያን በተገኙበት ሜይ 6 እና 12 ቀን 2018 በዴንማርክ እና በስቶክሆልም ከተሞች ተከብሯል፡፡

11

በስቶክሆልም በተካሄደው በዓል ለትግሉ ሰማእታት የህሊና ፀሎት ከተደረገ በኋላ በስዊድንና በሌሎች የኖርዲክ አገሮች የኢትዮዽያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ፕሮፌሰር መርጋ በቃና በአሉን አስመልክቶ ንግግር ያደረጉ ሲሆን፣ በንግግራቸውም ወታደራዊው የደርግ ስርዓት በወደቀ ማግስት ኢህአዴግ እና የሽግግር መንግስቱ በያዙት የተጠና መስመር አገራችን በርካቶች ከተነበዩት የመበተን አደጋ ድና ዛሬ ስልጣን ያለ አንዳች ችግር የሚሸጋገርበት ደረጃ ላይ መድረስዋን ገልፀዋል፡፡ አገራችን ላለፉት ጥቂት ዓመታት የተወሳሰቡ የፖለቲካ ችግር ውስጥ የቆየች መሆኗ የሚታወስ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ገዥው ፓርቲና መንግስት የተለያዩ ሪፎርሞችን በማካሄድ ችግሮቹን እየቀረፈ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

1

ክቡር አምባሳደር አያይዘውም ግንቦት 20 በፈጠረው አዲስ ምእራፍ በአገሪቱ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማሕበራዊ ድሎች እንዲመዘገቡ እድል ከመፍጠሩ ጋር ተያይዞ የህዝቡ የልማት ፍላጎት እያደገ መምጣቱንና   መንግስት በየጊዜው የሚነሱ የህዝቡን ፍላጎቶች ለማሟላትም ከሰፊው ህዝብ ጋር በቅንጅት ለመስራት ቁርጠኛ አቋም ይዞ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። በተመሳሳይ ከግንቦት 20 አብይ ትሩፋቶች አንዱ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግደብ መሆኑን ገልፀው የሀገራችን ህዝቦች ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ለመጀመር የመሰረት ድንጋይ የተጣለበትን ሰባተኛ ዓመት ክብረ በዓል “ታላቁ የህዳሴ ግድባችን የአገራችን ህብረ ዜማ! የህዳሴያችን ማማ!” በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ዝግጅቶች እያከበሩ ይገኛሉ። ግድቡ በሀገራችን ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች አንጡራ ሃብት እየተገነባ ያለ ሲሆን ሲጠናቀቅ ለአገራችንና ለተፋሰሱ አገራት የሚኖረው ፋይዳ የጎላ ነው። የሀገራችን ህዝቦች የዚህን ግድብ ግንባታ የዛሬ ሰባት ዓመት ሲጀምሩ፤ “እንደ ጀመርነው እንጨርሰዋለን” ብለው የነበረ ሲሆን አሁን ደግሞ ከ64 በመቶ በላይ አድርሰውት፣ “እንዳገባደድነው እንጨርሰዋለን” በማለት በአገር ቤትና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮዽያውያን እየተረባረቡ ይገኛሉ ብለዋል።

በመጨረሻም አገራችን በአጭር ጊዜ ህዳሴዋን እውን ለማድረግ የሚያስችል ብሔራዊ መግባባትን እየፈጠረ ያለ የሉዓላዊነታችን መገለጫ ፕሮጀክት በመሆኑ የህዳሴ ግድብ ቦንድ በመግዛት፣ በስጦታ በመለገስ እንዲሁም በቅርቡ የተጀመረው የህዳሴ ግድብ ቶምቦላ ሎተሪ በመግዛት ዳያስፖራው ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

በበአሉም በስቶክሆልም የህዳሴ ምክር ቤት ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ብርሀኑ ከበደ ሁሉም የኢትዮዽያ ብሄር ብሄረሰቦች በጋራ በመፈቃቀርና በመቻቻል መንፈስ የማንነታችን መገለጫ የሆነውን የህዳሴ ግድብ ግንባታ ለማጠናቀቅ በአንድነት ሆኖ የጀመረውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል መልእክታቸውን አስተላልፈዋል::

2

በበአሉም የህዳሴ ግድብ ወቅታዊ መረጃዎች አስመልክቶ ገለፃ ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል፡፡ የዳያስፖራ አባላት በሰጡት አስተያየት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴን ጨምሮ በአገር ውስጥ ለሚካሄዱ የልማት ስራዎች የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ፣ በአገራችን ለተደረገው ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ከፍተኛ አድናቆት እንዳላቸው የገለጹ ሲሆን ኤምባሲው የሚሰጣቸው አገልግሎቶች የበለጠ ቀልጣፋ እንዲሆኑ መሰራት እንዳለበት አንስተዋል። በበአሉም ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚውል ቦንድ እና ቶምቦላ  በመሸጥ  20, 820  /ሀያ ሺህ ስምንት መቶ ሀያ የአሜሪካን ዶላር/ ገቢ ማሰባሰብ ተችሏል፡፡

9