የዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ጉብኝት በኦስሎ

ethio norway 1የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከኖርዌይ አቻቸው ኤሪክሰን ሶርይዴ ጋር በሁለትዮሽና በአካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

ክብርት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ለዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤታቸውን አስጎብኝተዋቸዋል፡፡

ዶ/ር ወርቅነህ በኦስሎም ተንቀሳቅሰው የከተማውን ዋና ዋና ቦታዎች ቃኝተዋል፡፡

ክብርት ሚኒስትሯ በወቅቱ ለዶ/ር ወርቅነህ እንዳሉት፣ ኦስሎ ከመቶ አመት በኋላ ባለፈው ግንቦት ወር ከፍተኛውን ሙቀት ባስተናገደችበት ማግስት የተካሄደ ጉብኝት መሆኑ ጉብኝቱን ታሪካዊ ያደርገዋል፡፡

በተመሳሳይ ከኖርዌይ የፓርላማ የውጭ ግንኙነት ቋሚ ኮሚቴ ጋርም የሁለቱ አገሮች ግንኙነት በሚጠናከሩባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

የፓርላማ አባላቱ ኢትዮጵያን እንዲጎበኙ በክቡር ሚኒስትሩ ተጋብዘዋል፡፡ ግብዣውንም ተቀብለውታል፤ በአፍሪካ ከሚያደርጉት የሁለት አገሮች ጉብኝት ውስጥ አገራችን አንዷ ትሆናለች፡፡

ያራ ኢንተርናሽናል ኩባንያ በአገራችን የግብርናው መስክ ለመሰማራት ይፈልጋል።