አምባሳደር ድሪባ ኩማ ለስዊድን ንጉስ የሹመት ደብዳቤያቸውን አቀረቡ

1.2በስዊድንና በሌሎች የኖርዲክ ሀገራት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር በመሆን የተሾሙት ክቡር አምባሳደር  ድሪባ ኩማ እ.ኤ.አ ማርች 28 ቀን 2019 ለስዊድን ንጉስ Carl XVI Gustaf  የሹመት ደብዳቤያቸውን አቅርበዋል።

አምባሳደር ድሪባ ኩማ የሹመት ድብዳቤያቸውን ባቀረቡበት ወቅት ባደረጉት ንግግር በኢትዮጵያ እየተካሄደ ባለው የፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያ ሪፎርሞች እንዲሁም ኢትዮዽያ ከጐረቤት ሀገራት በቀጣናው ሰላም እንዲሰፍን እየተጫወተች ያለውን ሚና እና በሁለቱም ሀገራት መካከል  ያለው ረጅም ጊዜ ያስቆጠረ መልካም ግንኙነት  አንስተዋል፡፡

ንጉስ ካርል ጉስታፍ 6ኛው /Carl XVI Gustaf/  የኢትዮዽያ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት የኤሌክትሪክ ሀይልን በማመጨት ከራስዋ ባሻገር  ለጐረቤት ሀገራት ለማካፋፈል ታቅዶ እየተሰራ ያለው ስራ በጣም አበራታች መሆኑን፣ ከጐረቤት ሀገራት ጋርም የተፈጠረው መልካም ግንኙነት እንዲሁም በአረንጓዴ ልማት ዙሪያም እየተሰሩ ያሉ ሥራዎችን ጥሩ መሆኑን ገልፃዋል፡፡

2

ንጉሱም በተጨማሪ ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለችውን ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ለውጥ እንደሚደግፉ ገልፀው በቅርቡ በኢትዮጵያ በደረሰው የአውሮፕላን መከስከስ አደጋ ህይወታቸውን ላጡ ሰዎች የተሳመቸውን ሀዘን ገልጸዋል፡፡

ክቡር አምባሳደርም የሁለቱን አገሮች ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ ገልፀዋል።