በበፊንላንድ ሄልሲንኪ ከተማ የዳያስፖራ የውይይት መድረክ ተካሄደ

1በፊንላንድ ሄልሲንኪ ከተማ የዳያስፖራ የውይይት መድረክ ተካሄደ

የስቶክሆልም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ ከፊንላንድ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማሕበራት ጋር በመተባበር ሚያዚያ 26 ቀን 2011 ዓ.ም በሄልሲንኪ ከተማ የዳያስፖራ የውይይት መድረክ አካሂዷል። በመድረኩ ላይ ወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች፣ ዳያስፖራው በቴክኖሎጂና እውቀት ሽግግር፣ በኢንቬስትመንት እና በዳያስፖራ ትረስት ፈንድ ላይ ማድረግ ስለሚገባው አስተዋጽኦ የመነሻ ሀሳብ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል። ተሳታፊዎችም በአገራችን እየተደረገ ያለው ለውጥ የበለጠ እየሰፋና እየጠለቀ ተጠናክሮ እንዲቀጥልና የሰላምና መረጋጋት ጠንቅ የሆኑ መሠረታዊ ጉዳዮች በተለይም የህግ የበላይነት አለመከበር በአስቸኳይ መፈታት እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። በፊንላንድ የሚገኘውን የኢትዮጵያ የዳያስፖራ ማሕበረሰብ አንድነት ማጠናከር ይችል ዘንድ ከሁሉም ማሕበራትና የሀይማኖት ተቋማት የተውጣጡ ተወካዮች የታቀፉበት ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴም ተቋቁሟል።

2

Diaspora meeting takes place in Helsinki, Finland

Embassy of the F.D.R of Ethiopia in Stockholm in cooperation with Ethiopian diaspora communities in Finland have held a diaspora meeting in Helsinki on 4th of May 2019. A presentation was made on current national affairs, the role of Diaspora in technology and knowledge transfer, investment and diaspora trust fund. The attendants on their part underlined that the current undergoing reform shall further continue widening its scope and deepening its root. They also stressed that the issue of peace and stability should be given high priority and that the rule of law be respected by all. An ad hoc committee composed of representatives from all the associations and religious institutions was established in order to serve as a platform that brings together all diaspora groups in Helsinki.