በስዊድን፣ ኖርዌይ፣ ዴንማርክ፣ ፊንላንድና አይስላንድ ለምትገኙ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አባላት በሙሉ

Diaspora noticeክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ የሚገኙበት አውሮፓ አቀፍ የኢትዮጵያ ዳያስፓራ ኮንፍረንስ ይመለከታል፡-

ክቡር የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ የሚገኙበት ታላቅ የዳያስፖራ ኮንፍረንስ በጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ ኦክቶበር 31 ቀን 2018 ይካሄዳል።
በኮንፍረንሱ ከሁሉም የአውሮፓ አገራት የተውጣጡ የኢትዮጵያዊያን እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል። በኮንፍረንሱ በአገራችን እየተካሄደ ባለው ሁሌንተናዊ የለውጥ ጉዞ እና የዳያስፖራው ድርሻ ትኩረት ተሰጥቶት ሰፊ ውይይት ይካሄዳል።

በመሆኑም በኖርዲክ አገራት የምትገኙ የኢትዮጵያ የዳያስፖራ አባላት በሙሉ በእለቱ በፍራንክፈርት ከተማ በመገኘት በኮንፍረነሱን ላይ እንድትሳተፉ እና ስለ አገራችሁ ጉዳይ ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር እንድትወያዩ በክብር ተጋብዛችኋል።
የኮንፍረንሱ ቦታና ሰዓት ከታች የተጠቀሰው ሲሆን ለውጥ ካለ የምናሳውቃችቹ መሆኑን እንገልጻለን።

የኮንፍረነሱ ቦታ፡- Commerzbank Arena
Morfelder Landstrasse 362, 60528 Frankfurt am Main
ሰዓት፡ 13፡00 hrs