ማ ስ ታ ወ ቂ ያ : የክፍያ ጊዜው በደረሰ ቦንድ ምትክ በድጋሚ ለመግዛት የሚፈልጉ የዳያስፖራ አባላትን ይመለከታል

IMG_1629የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ቦንድ የገዙ አንዳንድ ኢደትዮጵያውያንና ትውልድ ኢትዮጵያውያን የገዙት ቦንድ የክፍያ ጊዜው ሲደርስ በምትኩ ሌላ ቦንድ ለመግዛት እንዲሁም ቦንድ የገዙበትን ገንዘብ በስጠታ መልክ ለመስጠት እንደሚፈልጉ በመግለጽ ይህንን በምን መልኩ ለማድረግ እንደሚችሉ ጥያቄ እያቀረቡ ይገኛሉ።

በመሆኑም የክፍያ ጊዜያቸው የደረሱ ቦንዶችን ተመላሽ በማድረግ በምትኩ ልላ መግዛት የሚፈልጉ የዳያስፖራ አባላት ቀደም ብለው የገዙትን ቦንድ ኦሪጅናል ሰርተፍኬት ለኤምባሲው በማስረከብ በምትኩ ሌላ ቦንድ ከዚህ በፊት በገዙት ዋጋ እና በተገኘው የወለድ መጠን የተዘጋጀ ቦንድ ይቀበላሉ። በሌላ በኩል የክፍያ ጊዜው የደረሰ ቦንድ ገንዘብ በስጦታ ለማበርከት የሚፈልጉ የዳያስፖራ አባላት በኦሪጅናል ሰርተፍኬቱ ጀርባ ገንዘቡን በስጦታ እንደሰጡ በመግለጽና በፊርማቸው በማረጋገጥ በስጦታ ማበርከት ይችላሉ።

በዚህ አጋጣሚ የግንባታ ሂደቱ እየተገባደደ ላለው ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በሀገር ፍቅር ስሜት ስታደርጉ ለነበራችሁት ድጋፍ ከፍ ያለ ምስጋና እያቀረብን፣ እስኪጠናቀቅ ድረስ ድጋፋችሁ እንዳይለየው ጥርያችንን እናቀርባለን።

ከሰላምታ ጋር

                                                                                                   ኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ

                                                                                                                                                                       ስቶክሆልም